
ሴፕቴምበር 16 ቀን 2023 ዓመተ ምሕረት በተደረገው የደመቀ ስነ ስርዓት ላይ ቤተክርስቲያኗ በውስጧ እያገለገሉ ከነበሩ ቅዱሳን መካከል ወንድም ጥሩ ሰው ወልደየስንና ወንድም በፈቃዱ በመጋቢነት የሾመች ሲሆን የአገልግሎት ምደባቸውንም አሳውቃለች፡፡ በዕለቱ በተደረገው መንፈሳዊ የሹመት ስነ ስርዓት የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ፣ ከካናዳ የተለያዩ ከተሞች የመጡ በርካታ ቅዱሳን ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መጋቢዎች ፣ ዘማሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የመጋቢዎችን ቃል የመግባትና የሹመት ስርዓት ያስፈጸሙት የቤተክርስቲያኗ ዋና መጋቢ ፓስተር መስፍን ብርሃኑ ሲሆኑ ለተሿሚዎቹ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት የሰጡት ደግሞ ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ከርሰቲያናት ሕብረት ዋና ጸሐፊ ናቸው፡፡
On September 16, 2023, Bethel Ethiopian Evangelical Church in Kitchener appointed two pastors among the saints who were serving in the church for a long time with a specified responsibility. In the Pastoral ordination ceremony held that day , the parishioners of the Church, Many Pastors, Gospel singers and ministers of the evangelical churches of Ethiopia and Eritrea were present.
Pastor Mesfen Berhanu, the Lead Pastor of the church, performed the Ordination process of the appointment ceremony of the pastors, followed by Pastor Yohannes Teffera, the general secretary of the Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada who distributed the certificate to the appointees.
ዕሁድ ሴፕቴምበር 24 ቀን 2023 ዓመተ በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረትን በዋና ጸሐፊነት ለማገልገል በቅቡ ከኖርዌይ ወደ ካናዳ ለመጡት ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራና ለባለቤታቸው ለእህት አሰለፈች አሰፋ በጉባኤ በመጸለይ ኃላፊነቱን የማስረከብ ሥነ-ሥርዓት ተደርጓል፡፡
ኃለፊነቱን በማረካከቡ ሂደት የሕብረቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በካልጋሪ የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን መጋቢ ፓስተር ወርቅነህ ሞገሴ ኅብረቱን በመወከል ፓስተር ዮሐንስ ተፈራን የሚከተለውን ቃል አስገብተዋል፡፡
“ እኔ ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ ከባለቤቴ ከእህት አሰለፈች አሰፋ ጋር ሆኜ ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በከናዳ የተሰጠኝን የሕብረቱን ጽሕፈት ቤት ኃላፊነት ስራ በታማኝነትና በትጋት ያለ ምንም ልዩነት ጌታ በሰጠኝ ጸጋ ሁሉ ለማገልገል ቃል እገባለሁ፡፡ ጊዜዬን የግል ሕይወቴንና ምስክርነቴን እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመወጣት ቃል እገባለሁ፡፡ ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ እንደሚረዳኝ አምናለሁ፡፡” በማለት በጉባኤው ፊት አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱ በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አባል ቤተክርስቲያናትን በመወከል ከመላው ካናዳ የተገኙ መጋቢዎችና የቤተ ክርስቲያናት ሽማግሌዎች ዕጅ በመጫን በጸሎትና በምስጋና የዋና ጸሐፊውንና የባለቤታቸውን የአገልግሎት ስምሪት በጌታ ፊት በጸሎት አቅርበዋል፡፡
የወቅቱ የ2023 ዓመተ ምሕረት የመሪዎች አመታዊ ስብሰባ የኅብረቱ 30ኛ ዓመት የተከበረበትና ለበርካታ ዓመታት ሲጸለይበት የነበረው በሙሉ ጊዜ ሕብረቱን የሚመራ አገልጋይ የተመደበበት ወቅት ላይ የተደረገ በመሆኑ ይህን ስብሰባ የተለዬ እንደሚያደርገው በርካታ አባላት ተናግረዋል፡፡ ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራ መልካም የአገልግሎት ዘመን ለመመኘት የተዘጋጀውን ኬክ ፓስተሩ ከባለቤታቸው ጋር በመቁረስ ስብሰባው በጸሎትና በፓስተር /ዶከተር ኤፍሬም ላዕከ ማርያም በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ቡራኬ ጌታ ያስተማረውን ጸሎት በዜማ በመጸለይ ተጠናቋል፡፡
ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመረከብ ከኖርዌይ ወደ ካናዳ ከመምጣታቸው በፊት
በኖርዌይ ኦስሎ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክተርስቲያን ዋና መጋቢ፣በኢንተርኔት የወንጌል ስርጪት ፈር ቀዳጅ የሆነውና አሁንም 24 ሰዓት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው በፓል ቶክ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሁሉም ክፍል ባለራዕይና መስራች፣
የመረብ አለም አቀፍ ክርስቲያናዊ መጽሔት አዘጋጅና አሳታሚ፣በሰሜን አውሮፓ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ከርስቲያናት ሕብረት ሰብሳቢ፣ በኖርዌይ የኢትዮጵያና ኤርትራውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ዋና ጸሐፊ፣
በአውሮፓ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን መጋቢዎች ሕብረት ዋና ጸሐፊ፣ በኢትዮጵያውያን የዲስፖራ አብያተከርስቲያናትን ለማደራጀት ላይ ባለው ግብረ ኃይል አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፣ከኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ለአውሮፓና ለምድራችን ኢትዮጵያ የሚጸለየውን ሳምንታዊ የጸሎት አገልግሎት አስጀማሪና አስተባባሪ በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡ ወደ ኖርዌይ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በየመን በስደተኛነት በኖሩባቸው ዓመታት ሰነዓ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ሽማግሌና በሰነዓ ኢንተርናሽናል የክርስቲያኖች ካውንስል ስራ አመራር አባልና በመሆን ማገልገላቸውም ታውቋል፡፡
ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ በኖርዌይ ታዋቂ ከሆነው MF Norwegian School of Theology, በሃይማኖት ሕብረተሰብና አለምአቀፍ ጉዳዮች (Religion Society and Global Issues) የማስተርስ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከኖርዌይ ከተለያዩ ኮሌጆች በሜዲያ፣ ሕዝብ ግንኙነት፣ በስነ መለኮትና አስተዳደር በርካታ ዲፕሎማዎችና የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፡፡
ከኢትዮጵያ ከመውጣታቸው በፊትም በቀድሞዋ ሶቪዬት ሕብረት ፣ በሕንድና በሆላንድ የወደብ አስተዳደር ሙያ የሰለጠኑ ሲሆን በተለያዩ አለምአቀፍ ኮንፈረንሶችና ስልጠናዎች ላይ የተሳተፉ ነበሩ፡፡ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ የወጣትነት ዕድሜያቸውን ስላሳለፉባት አሰብ ወደብና ከተማ እንዲሁም በመካከሉ ስለኖሩበትና እንደ ቤተሰብ ስለሚቆጥሩት የአፋር ሕዝብ ታሪክ የሚያወሳ “ አሰብ ቀይ ባሕርና ወደባችን በዚያን ጊዜ “ የተሰኘ መጽሐፍ አበርክተዋል፡፡ በተጨማሪም በ22 ዓመታት የኢንተርኔት አገልግሎት ተሞክሮና በሕይወት ልምዳቸው ላይ በመመርኮዝ “ሥነ ሳቅ” የተሰኘ መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡ በጠቅላላው ሁለት ዳጎስ ያሉ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁ ሲሆን በቅርቡም ተጨማሪ መጻሕፍትን ለንባብ ለማብቃት በዝግጀት ላይ አንዳሉም ለማወቅ ተችሏል ፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራ መልካም የአገልግሎት ጊዜና ለሕብረቱ ራዕይና ዕቅድ ስኬትን አንመኛለን፡፡
On Sunday, September 24th, 2023, an inauguration ceremony and prayer were held for Pastor Yohannes Tefera and his wife, Sister Asselefech Asefa, who relocated from Norway to Canada to serve as the General Secretary of the Union of Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada.
In the process of taking responsibility on behalf of the Fellowship, Pastor Workneh Mogese, a member of the Union's Executive Committee and pastor of the Philadelphia Church in Calgary, had Pastor Yohannes Tefera take an oath by asking him to repeat the following statement: "I, Pastor Yohannes Tefera, together with my wife Asselfech Asefa, promise to faithfully and diligently serve the responsibilities of the office of the Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada, without exception, with all the grace God has given me. I commit to living out my time, personal life, and testimony according to God's word. I believe that God will help me in this." He confirmed this commitment in front of the assembly.
On that day, pastors and church elders from all over Canada, representing the member churches of the Ethiopian Evangelical Churches Union in Canada, laid hands, offered prayers, and expressed thanks for the ministry of the Secretary General and his wife before the Lord.
Many members noted that the annual meeting of leaders in 2023 coincided with celebrating the union's 30th anniversary and the appointment of a full-time minister to lead the union. The pastor and his wife cut the cake prepared to wish them a successful term of service.
Pastor Yohannes had decided to take on this great responsibility in Canada before coming from Norway. He was the head pastor of the Ethiopian Evangelical Church in Oslo, Norway, the visionary and founder of Pal Talk, a pioneer in Internet evangelism that continues to provide 24-hour services for all classes of Ethiopian Christians.
Before he moved to Canada from Norway, Pastor Yohannes served as the editor and publisher of Mereb International Christian Amharic Magazine, the Chairman of the Union of Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Scandinavia, and the General Secretary of the Union of Ethiopian and Eritrean Churches in Norway.
He also held the position of General Secretary of the Union of European Ethiopian Evangelical Pastors, was a member of the task force coordinating committee for organizing Ethiopian Diaspora churches, and served as the coordinator of the weekly prayer service that prays for Europe and Ethiopia, in cooperation with Elshadai Television. Earlier before moving to Norway, he served as an elder of the Ethiopian Evangelical Church in Sana'a and was a member of the Sana'a International Christians fellowship during his years as a refugee in Yemen.
Pastor Yohannes Tefera received a master's degree in Religion, Society, and Global Issues from the renowned MF Norwegian School of Theology. He also holds several diplomas in media, public relations, including a bachelor's degree in theology and Administration from HLT in Oslo, Norway.
Before leaving Ethiopia, he received training and studied in the former Soviet Union, India, and Holland, and participated in various international conferences and training programs. Pastor Yohannes Tefera authored two books, including "Gelotology, human behaviours, and characters with humorous in 5 categories based on his 22 years of internet service and real-life experiences. It is known that he is currently working on another book.
On this occasion, we extend our best wishes to Pastor Yohannes Tefera for a successful term of service and for achieving his vision and plans for the Fellowship he is assigned to serve.
Research Center

በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ ካለፈው ሰኞ ሴፕቴምበር 18 ቀን ጀምሮ በFair Havens Camp & Conference Centre Beaverton, Ontario L0K 1A0 Canada የቀጠለ ሲሆን ስብሰባው የፊታችን ዐርብ ሴፕቴምበር 22 እኩለ ቀን ላይ ይጠናቀቃል፡፡
በመቀጠልም በቶሮንቶ የሚገኙት በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አባል አብያተክርስቲያናት አዘጋጀነት የተዘጋጀው የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ይደረጋል፡፡
ዐርብ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ በቃል የሚያገለገልት ፓስተር መልኬ ነጋሽ በዊኒፔግ የሕያው ወንጌል ቤተክርስቲን ዋና መጋቢና የወቅቱ የሕብረቱ ቦርድ ሰብሳቢ ናቸው፡፡
ቅዳሜ የወቅቱ የሕብረቱ ቦርድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት ፓስተር ወርቅነህ ሞገሴ በካልጋሪ የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢና ፓስተር ተረፈ ሰረቀ በኤድመንተን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ኮንፈረንሱን በቃል ያገለግላሉ፡፡
በመጨረሻም ዕሁድ ሴፕቴምበር 24 ቀን 2023 ዓመተ ምሕረት በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ጉባኤ ላይ በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረትን በዋና ጸሐፊነት ለማገልገል በቅቡ ከኖርዌይ ወደ ካናዳ ለመጡት ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራና ለባለቤታቸው ለእህት አሰለፈች አሰፋ በጉባኤ በመጸለይ ኃላፊነቱን የማስረከብ ሥነ-ሥርዓት ይደረጋል፡፡
በዕለቱ የእግዚአብሔርን ቃል በማቅረብ የሚያገለግሉት ፓስተር ቻላቸው እሸቱ በካልጋሪ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢና የወቅቱ የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡
በ30ኛው የሕብረቱ አመታዊ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ከመላው ካናዳ የተገኙ መጋቢዎችና የቤተክርስቲያን መሪዎች በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ገባኤ ላይ በመገኘት ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራና ለባለቤታቸው ለእህት አሰለፈች አሰፋ በሕብረት በመጸለይ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ይሆናል;;
በዚህ አጋጣሚ በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ስር አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህ 30ኛ ዐመታዊ ስብሰባ እንዲሳካ ያልተቆጠበ ጥረት ያደረጉትን በቶሮንቶ ከተማ የሚገኙትን አባል ቤተክርስቲያናትና ኮንፈረንሱን በማስተናገድና ለጉባዔው ተሳታፊዎች በራቸውን በመክፈት ያልተቆጠበ ድጋፍ ላበረከቱት እንዲሁም ለሕብረቱ ዋና ጸሐፊ የሚሆን ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት በማዘጋጀት ለተባበሩት በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም ለሕብረቱ 30ኛ አመት የመሪዎች ስብሰባ በቤተክርስቲያን አመራርና በመሪዎች ሚና ዙሪያ ጠቃሚ ትምሕርት ያስተማሩትን ፓስተር በድሉ ይርጋን በዳላስ ቴክሳስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርቲያን ዋና መጋቢን እግዘአብሔር አብዝቶ ይባርክዎ እንላለን፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ የፊታችን ሰኞ ሴፕቴምበር 18 ቀን 2023 ዓመተ ምሕረት በቶሮንቶ ከተማ ይጀመራል፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በተለያዩ የካናዳ ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወደ ቶሮንቶ ይመጣሉ፡፡ ስብሰባው ሰኞ ሴፕቴምበር 18 ቀን ተጀምሮ ዐርብ ሴፕቴምበር 22 እኩለ ቀን ላይ ይጠናቀቃል፡፡ ሕብረቱ ዓመታዊ ስብሰባው በሚስተናገድበት ከተማ ኮንፈረንስ በማድረግ የአምልኮና የምስጋና ጊዜ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም መሰረት ዐርብ ምሽትአንድ ፕሮግራም ቅዳሜ ከሰዓት በኋላና ምሽት 2 ፕሮግራሞች ይደረጋሉ፡፡
የዘንድሮውን ስብሰባ የተለዬ የሚያደርገው ለዓመታት የሕብረቱን ስራ በሙሉ ጊዜ የሚያስተባብር አገልጋይ ጌታ እንዲሰጥ ሲጸለይበት የነበረው የጸሎት ጥያቄ የተመለሰበት መሆኑ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡት የሕብረቱ መሪዎች ከቶርንቶ ቅዱሳን ጋር በመሆን ለፓስተር ዮሐንስ ተፈራና ለባለቤቱ በመጸለይ ‹ዕጅ በመጫን ኃላፊነቱን በኦፊሲየል ያስጀምራሉ፡፡ ይህም የጸሎት ፕሮግራም ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ሴፕቴምበር 24 ቀን ዕሁድ ጧት በቶሮንቶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ጉባኤ ላይ ይከናወናል፡፡
በዚሁ 30ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሪዎች ወቅታዊ ትምሕርት እንዲያቀርቡ የተጋበዙት ፓስተር በድሉ ይርጋ በዳላስ ቴክሳስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ናቸው፡፡