የያቤሎ የመጠጥ ውሃ ቁፈራ ፕሮጄክት
በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የገነዘብ ድጋፍ በቦረና ዞን በያቤሎ አቅራቢያ በምትገኘው በጐሞሌ ወረዳ ሀሊሳ፣ ጢሌ ጋቦ እና ሀሮ ዳጋይ በሚባሉት ቀበሌዎች 3 የውሃ ጉድጓዶች ተቆፍሮ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲረከቡ ተደርጓል፡፡የውሃውን ጉድጓድ ቁፋሮ አንዲያከናውን ኮንትራት የተሰጠው LM ኢንተርናሸናል የተባለ ድርጅት ነው፡፡ ይህን የዕርዳታ አገልግሎት አስመልክቶ የተጠናቀረውን የፊልም ዘገባ ተመልክቱት፡፡