Research Center
Bill - C9 በፓርላማው ሕግ ሆኖ ከመጽደቅ እንዲቆይ ተወስኗል፡፡ ዝርዝር ጉዳዩን ሐሙስ ከባለሙያዎች አንሰማለን፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ሊጸድቅ ተቃርቦ የነበረው Bill - C9 ከተለያዩ አቅጣጫዎች (የእኛን ጨምሮ) ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠመው ለጊዜው በፓርላማው ከመጽደቅ እንዲቆይ ተወስኗል፡፡ ለእኛ የጸሎታችን መልስ ነው እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ ነገር ግን በፓርላማው ከመጽደቅ እንዲቆይ ተወስኗል ማለት እንደገና ጉዳዩ የመነሳት ዕድል አለው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ሐሙስ ( ፊበረዋሪ 5 8፡00 PM Eastern ) ከ3 ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጋር ስለ Bill - C9 በሚደረገው ውይይትና ወደ ፊትም ማድረግ ስላለብን ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ እንድንጨብጥ በሰዓቱ እንድንገኝ በማክበር እናሳስባለን፡፡
በካናዳ ሕግ ሆኖ ሊወጣ ያለው Bill C-9 በቤተክርስቲያን ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄ ብዙ ቤተእምነቶችንና የእምነት ተቋማትን እያነጋገረ ነው፡፡ ብዙዎች ይህ ሕግ የእምነትን ነጻነት እንዳይገድብ በመፍራት ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትርና ለአካባቢያቸው የፓርላማ ተወካዮቻቸው ጠበቅ ያለ ደብዳቤ እየጻፉ ነው፡፡ እኛም ከሕግ አንጻር ተገቢውን ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳን ዘንድ በቶሮንቶ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጋር ቀጥተኛ ጥያቄና መልስን የሚየካትት ውይይት በZoom አዘጋጅተናል፡፡ ሁላችንም የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች የፊታችን ሐሙስ ፌብርዋሪ 5 ቀን 2026 ዓመተ ምሕረት ከምሽቱ 8- 10 PM Eastern በምናደርገው የ Zoom ስብሰባ ላይ እንድንገኝ ጥሪያችንን አናስታላልፋለን፡፡
በተጨማሪም ለባለሙያዎቹ እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉት ጥያቄ ካላችሁ አስቀድማችሁ ብታሳውቁን ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳናል፡፡በተጨማሪም በማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያገለገሉ ያሉ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ቢካፈሉ ጠቃሚ ስለሆነ ጥሪውን ቢተላለፍላቸው መልካም መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡