አዲስ መጽሐፍ ለንባብ
በካናዳ የኢትዮጵያውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅበረት አባል የሆነችው በቫንኩበር የጸጋ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መጋቢ የሆኑት ፓስተር/ዶ/ር ወርቁ መኮንን “የግብይትና የለውጥ አስተዳደር በኢትዮጵያ”/ “Transformational & Transactional Church Governance " በሚል ርዕስ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ሁለት መጻሕፍት ለንባብ አብቅተዋል፡፡
የኅብረቱ አባል ቤተክርስቲያን መጋቢዎች ከመደበኛው የቃለ እግዚአብሔር መግቦት አገልግሎት በተጨማሪ በተገኙት ዕድሎች ሁሉ በመጠቀም ዕውቀትን ለማካፈል የሚያደርጉት ጥረት የሚያስደስትና ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ኅብረቱ ፓስተር/ዶ/ር ወርቁ መኮንንን ለዚህ ስኬት እንኳን ደስ አለዎ እያለ አባል ቤተክርስቲያናትም መጻሕፍቱን በማስተዋወቅና በስርጪቱ ዘርፍም በማገዝ እንዲተባበሩ ያሳስባል፡፡