News and Updates

በካናዳ ሕግ ሆኖ ሊወጣ ያለው Bill C-9 በቤተክርስቲያን ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል?

በካናዳ ሕግ ሆኖ ሊወጣ ያለው Bill C-9 በቤተክርስቲያን ላይ  ምን ዓይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል?

በካናዳ ሕግ ሆኖ ሊወጣ ያለው Bill C-9 በቤተክርስቲያን ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄ ብዙ ቤተእምነቶችንና የእምነት ተቋማትን እያነጋገረ ነው፡፡ ብዙዎች ይህ ሕግ የእምነትን ነጻነት እንዳይገድብ በመፍራት ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትርና ለአካባቢያቸው የፓርላማ ተወካዮቻቸው ጠበቅ ያለ ደብዳቤ እየጻፉ ነው፡፡ እኛም ከሕግ አንጻር ተገቢውን ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳን ዘንድ በቶሮንቶ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጋር ቀጥተኛ ጥያቄና መልስን የሚየካትት  ውይይት በZoom አዘጋጅተናል፡፡ ሁላችንም የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች የፊታችን ሐሙስ ፌብርዋሪ  5 ቀን 2026 ዓመተ ምሕረት ከምሽቱ 8- 10 PM Eastern በምናደርገው የ Zoom ስብሰባ ላይ እንድንገኝ ጥሪያችንን አናስታላልፋለን፡፡

በተጨማሪም ለባለሙያዎቹ  እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉት ጥያቄ ካላችሁ  አስቀድማችሁ ብታሳውቁን ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳናል፡፡በተጨማሪም  በማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያገለገሉ ያሉ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ቢካፈሉ ጠቃሚ ስለሆነ ጥሪውን ቢተላለፍላቸው መልካም መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡