Mission & Charity የወንጌል ተልዕኮና የዕርዳታ ድጋፍ
የሕብረታችን የዕርዳታ ድጋፍ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት በካናዳ ከተቋቋመ 30 ዓመታት አሳልፏል፡፡ ሕብረቱና የሕብረቱ አባል አብያተክርስቲያናት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ለደረሱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የበኩላቸውን ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በተጨማሪም ለአስፈላጊ የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎች፣ የወንጌል ስርጭትና ለመሳሰሉት ከፍተኛ ድጋፍ በየጊዜው ለግሰዋል፡፡
በቅርብ ከተከናወኑት የልግስና ተግባራት ውስጥ
- በቦረና አካባቢ በደረሰው ድርቅ ዕርዳታ የሚውል $45, 125 የካናዳ ዶላር በማዋጣት ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ የሚችል ሶስት የመጠጥና የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ በመከናወን ላይ ነው፡፡
- በትግራይና በመተከል ለደረሰ መፈናቀል የድጋፍ እርዳታ $48,200 የካናዳ ዶላር ተሰብስቦ ተልኳል፡፡
- በወሎና አፋር ክልል ለ 25 አብያተ ክርስቲያናት $117,000 የካናዳ ዶላር ተዋጥቷል
- ለኮቪድ 19 (Covid 19) ወረርሽኝ ዕርዳታ $211, 347 የካናዳ ዶላር ተሰብስቦ የተላከ ሲሆን በአጠቃላይ ከተረጂዎች የተላከውን ሪፖርትና መረጃ በቀጣይ እናሳውቃለን፡፡