የያቤሎ የመጠጥ ውሃ ቁፈራ ፕሮጄክት

በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት  የገነዘብ ድጋፍ በቦረና ዞን በያቤሎ አቅራቢያ በምትገኘው በጐሞሌ ወረዳ ሀሊሳ፣ ጢሌ ጋቦ እና ሀሮ ዳጋይ በሚባሉት ቀበሌዎች 3 የውሃ ጉድጓዶች ተቆፍሮ  የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲረከቡ ተደርጓል፡፡የውሃውን  ጉድጓድ ቁፋሮ አንዲያከናውን ኮንትራት የተሰጠው LM  ኢንተርናሸናል የተባለ ድርጅት ነው፡፡ ይህን   የዕርዳታ አገልግሎት  አስመልክቶ የተጠናቀረውን የፊልም ዘገባ ተመልክቱት፡፡
 

 

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በካናዳ የመጋቢዎችና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወርሃዊ ስብስባ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በካናዳ የመጋቢዎችና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወርሃዊ ስብስባ

የካናዳ ሕግና የቤተክርስቲያን መሪዎች  ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተዘጋጀ ትምሕርታዊ ሴሚናር

Research Center

የፓስተር ሊንዳ ባልድዊን የ21 አመት አገልግሎት ማጠናቀቂያና ሽግግር

በቶሮንቶ የምትገኘውን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን  ላለፉት 21 ዓመታት የልጆችና የወጣቶች  አገልግሎትን በታማኝነት፣  በሙሉ ትጋትና በግምባር ቀደምትነት ሲያገለግሉ የቆዩትን የፓስተር ሊንዳ የ21 አመት አገልግሎትን ማጠናቀቂያና ሽግግርን በተመለከተ የደመቀ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሠረት  January 21,2024 በቤተክርስቲያኗ ልዩ የእራት ምሽትና የምስክርነት ጊዜ ተከናውኗል ። በምሽቱ ለፓስተር ሊንዳ ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተበረከተ ሲሆን  ስለአገልግሎታቸው ፍሬ  በርካታ ምስክርነት ቀርቧል፡፡ ፓስተር ሊንዳም በእግዚአብሔር ምሪት ወደ አገልግሎቱ መግባታቸውን ጊዜውም ሲደርስ አሁንም በእግዚአብሔር ምሪት ለተተኪያቸው ማስረከባቸውን ገልፀዋል። በዝግጀቱ ላይ ከቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና አባላት በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው የቶሮንቶ ከተማ የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት መሪዎችና መጋቢዎች የተለያዩ እህት አብያተክርስቲያናት መሪዎች እንዲሁም ከፓስተር ሊንዳ ጋር ያገለገሉና ቤተሰብ የሆኑ የኪዊንስ ዌይ ቶሮንቶ ካቴድራል አባላት ተገኝተው ለበኣሉ ድምቀት ሰጥተዋል፡፡በምሽቱ ፕሮግራም ላይ የቤተክርሰቲያኗ ዋና መጋቢ ፓስተር/ዶር ኤፍሬም ላእከ ማርያም የፓስተር ሊንዳ ባልድዊንን የሕይወት ታሪክና አገልግሎት አስመልክቶ በፎቶግራፍ የተደገፈ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የቤተከርስቲያኗ የሽማግሌዎች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ድልነሳሁ ቸኮለ እንደዚሁ በቤተክርቲያኗ አባላት ስም የምስጋና ንግግር አድርገው የተዘጋጀውን ስጦታ አበርክተዋል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ የነበረውን የቃልና የዝማሬ አገልግሎት ያበረከቱት  ከሕጻንነት ዕድሜ ጀምረው በፓስተር ሊንዳ እየተማሩና እየተኮተኮቱ ያደጉ ወጣቶች ሲሆኑ በተለያዬ የዕድሜ ክልሉ ያሉ ልጆች በየተወካዮቻቸው አማካይነት ያቀረቡት ምስጋና በጣም ልብ የሚነካ አስደሳች ትዕይንት ነበር፡፡

የካናዳ የኢትጵያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በቶሮንቶ የተደረገው ይህ አስደናቂ ሽግግርና በተለይም ፓስተር ሊንዳ ባልድዊን ላለፉት 21 ዓመታት ያፈሯቸው ወጣቶች በቶሮንቶ ከተማ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በመላው ካናዳ ከተሞች ተበትነው ለቤተክርስቲያን አጋዥ ኃይሎች እንደሚሆኑ በማመን በበዓሉ ላይ ተገኘተን የአበባ ስጦታና የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈናል፡፡

A New song dedication Program at Elshalom Toronto

That sounds incredible! Music has a way of bringing people together for a meaningful cause, especially when it supports something as significant as acquiring a Church building. Blen Markos's song dedication program seems like it was a beautiful way to contribute to the community and the Church's goals. May God bless her and her family.