News and Updates

የፓስተር ሊንዳ ባልድዊን የ21 አመት አገልግሎት ማጠናቀቂያና ሽግግር

በቶሮንቶ የምትገኘውን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን  ላለፉት 21 ዓመታት የልጆችና የወጣቶች  አገልግሎትን በታማኝነት፣  በሙሉ ትጋትና በግምባር ቀደምትነት ሲያገለግሉ የቆዩትን የፓስተር ሊንዳ የ21 አመት አገልግሎትን ማጠናቀቂያና ሽግግርን በተመለከተ የደመቀ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሠረት  January 21,2024 በቤተክርስቲያኗ ልዩ የእራት ምሽትና የምስክርነት ጊዜ ተከናውኗል ። በምሽቱ ለፓስተር ሊንዳ ልዩ ልዩ ስጦታዎች የተበረከተ ሲሆን  ስለአገልግሎታቸው ፍሬ  በርካታ ምስክርነት ቀርቧል፡፡ ፓስተር ሊንዳም በእግዚአብሔር ምሪት ወደ አገልግሎቱ መግባታቸውን ጊዜውም ሲደርስ አሁንም በእግዚአብሔር ምሪት ለተተኪያቸው ማስረከባቸውን ገልፀዋል። በዝግጀቱ ላይ ከቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና አባላት በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው የቶሮንቶ ከተማ የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት መሪዎችና መጋቢዎች የተለያዩ እህት አብያተክርስቲያናት መሪዎች እንዲሁም ከፓስተር ሊንዳ ጋር ያገለገሉና ቤተሰብ የሆኑ የኪዊንስ ዌይ ቶሮንቶ ካቴድራል አባላት ተገኝተው ለበኣሉ ድምቀት ሰጥተዋል፡፡በምሽቱ ፕሮግራም ላይ የቤተክርሰቲያኗ ዋና መጋቢ ፓስተር/ዶር ኤፍሬም ላእከ ማርያም የፓስተር ሊንዳ ባልድዊንን የሕይወት ታሪክና አገልግሎት አስመልክቶ በፎቶግራፍ የተደገፈ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የቤተከርስቲያኗ የሽማግሌዎች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ድልነሳሁ ቸኮለ እንደዚሁ በቤተክርቲያኗ አባላት ስም የምስጋና ንግግር አድርገው የተዘጋጀውን ስጦታ አበርክተዋል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ የነበረውን የቃልና የዝማሬ አገልግሎት ያበረከቱት  ከሕጻንነት ዕድሜ ጀምረው በፓስተር ሊንዳ እየተማሩና እየተኮተኮቱ ያደጉ ወጣቶች ሲሆኑ በተለያዬ የዕድሜ ክልሉ ያሉ ልጆች በየተወካዮቻቸው አማካይነት ያቀረቡት ምስጋና በጣም ልብ የሚነካ አስደሳች ትዕይንት ነበር፡፡

የካናዳ የኢትጵያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በቶሮንቶ የተደረገው ይህ አስደናቂ ሽግግርና በተለይም ፓስተር ሊንዳ ባልድዊን ላለፉት 21 ዓመታት ያፈሯቸው ወጣቶች በቶሮንቶ ከተማ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በመላው ካናዳ ከተሞች ተበትነው ለቤተክርስቲያን አጋዥ ኃይሎች እንደሚሆኑ በማመን በበዓሉ ላይ ተገኘተን የአበባ ስጦታና የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈናል፡፡

A New song dedication Program at Elshalom Toronto

That sounds incredible! Music has a way of bringing people together for a meaningful cause, especially when it supports something as significant as acquiring a Church building. Blen Markos's song dedication program seems like it was a beautiful way to contribute to the community and the Church's goals. May God bless her and her family.

Research Center

የካሴት ምረቃና ሽያጭ

የካሴት ምረቃና ሽያጭ

ከካሴቱ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በሙሉ በሙሉ ለቤተክርስቲያኗ በስጦታ የተሰጠ ሲሆን ቤተክርስቲያኗ አሁን የምታመልክበት የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ባለቤቶቹ ሊሸጡት እንደሚችሉ የሚያሳዩ ሁኔታዎች አሉ።  የኤል ሻሎም ቤተክርስቲያን ቅዱሳን ለዚህ መልካም ዕድል ለመዘጋጀትና ለመግዛት እንዲችሉ የገንዘብ አቅም ለማሰባሰብ አስበው  ሁላችንም  የክርስቶስ አካል የሆንን ሁሉ ካሴቱን በመግዛት እንድንተባበር ጠይቀዋል።

በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አዲስ የአመራር አባላትን መረጠ፡፡

በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ኦከቶበር 10 ቀን 2023 ባደረገው የመሪዎች ስብሳ በየደረጃው አዲስ የአመራር አባላትን መርጧል፡፡ በሕብረቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9; መሠረት በየ3 አመቱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ 3 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ለምስራቅና ምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ለእያንዳንዳቸው 3 መሪዎችን ይመርጣል፡፡

በዚህም መሰረት በመተዳደሪያ ደንቡ  አንቀጽ 10;2 ለ2 ተከታታይ ስራ ዘመን ባገለገሉት በፓስተር መልኬ ነጋሽ  ምትክ ፓስተር ደረጀ ኃይለየሱስን የሕብረቱ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል፡፡   ፓስተር ተረፈ ሰረቀ የሕብረቱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ

በተጨማሪም  ለሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት

ፓስተር ቻላቸው እሽቱ

ፓስተር ዶ/ር ኤፍሬም ላዕከ ማርያም

ፓስተር አማረ ተክሉ

  • ለምስራቅ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት

 ፓስተር መስፍን ብርሃኑ

ፓስተር ኢያሱ ተስፋዬ

ፓስተር  ዶ/ር ግርማ በቀለ

  • ለምዕራብ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት መሪነት

ፓስተር ወርቅነህ ሞገሴ

ፓስተር ዱባ ገልገሌ

ፓስተር ዶ/ር ወርቁ መኮንን ሆነው ተመርጠዋል። 

ለአዲሶቹ ተመራጮች መልካም የስራ ዘመን እየተመኘን በቅንነት አገልገለው ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለቀጣይ መሪዎች ላስረከቡት መሪዎቻችን ደግሞ ልባዊ ምስጋናችንን  እናቀርባለን፡፡